በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞቅዲሾ ስታዲየም ውስጥ ሰፍሮ የነበረው የተመድ ሚሽን /አሚሶም/ ለቆ ወጣ


Mogadishu, Somalia
Mogadishu, Somalia

ሶማልያ የሚገኘውና ሞቅዲሾ ስታዲየም ውስጥ ሰፍሮ የነበረው የተመድ ሚሽን አሚሶም ከስፖርት ሜዳው ለቆ መውጣቱ ተገለፀ።

ሶማልያ የሚገኘውና ሞቅዲሾ ስታዲየም ውስጥ ሰፍሮ የነበረው የተመድ ሚሽን /አሚሶም/ ከስፖርት ሜዳው ለቆ መውጣቱ ተገለፀ።

“አፍሪካ ሕብረት ሚሽን በመጨረሻ የወጣቱን ድምፅ ሰምቶ ብሔራዊው ስታዲየም እንደገና ለስፖርቱ እንቅስቃሴ እንዲውል ሜዳውን በመልቀቁ እጅግ ተደስተናል” ሲሉ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትሯ ከሃዲጆ ሞሐመድ በርክክቡ ሥነ ሥርዓት ላይ ተናግረዋል።

የሶማልያው ፕሬዚደንት ሞሐመድ አብዱላሂ (ፎርማጆ) በበኩላቸው፣ መንግሥት የጦር ቀጣና ሆኖ የቆየውንና በእጅጉ የተጎዳውን ስታዲየም ለሀገሪቱ የስፖርት እንቅስቃሴ ለማዋል ጥረት እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

ይህ እአአ በ1970ዎቹ በቻይናውያን የተገነባው ታዲየም ከወታደራዊ ልምምድ ሌላ ምንም ዓይነት የአትሌቲክስ እንቅስቃሴ እንዳላስተናገደ ይታወቃል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG