በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሞቃዲሾ ከንቲባን ህይወት ያጠፋ ፍንዳታ የፈፀመችው አይነ ስውር ሴት


የሶማልያ መንግሥት በተናገረው መሰረት በቅርቡ የሞቃዲሾ ከንቲባን ህይወት ያጠፋውን ፍንዳታ የፈፀመችው በሌላ ሴት የተመራች አይነ-ስውር ሴት ነች።

የሶማልያ መንግሥት ዛሬ ያወጣው መግለጫ፣ ሁለቱ ሴቶች ተገቢ የማጣርያ ሂዳት ሳይደረግባቸው በከተማይቱ የመንግሥት መሥርያ ቤት ተቀጥረው ይሰሩ እንደነበር ገልጿል።

ሁለቱም ሴቶች በሀገሪቱ በአሸባሪዎች ቁጥጥር ሥር ባሉት ቦታዎች ለመዘዋወር በአንድ ወር ውስጥ በተከታታይ ዕረፍት ወስደው እንደነበር መግለጫው ጠቁሟል።

አል ሸባብ እአአ ባለፈው ሃምሌ 24 ቀን ለተፈፀመው ፍንዳታ ኃላፊነት መውሰዱ ይታወሳል። የሞቃዲሾ ከንቲባ አብዲራሕማን ኡመር ኦስማንን ያካተቱ ሌሎች የአስተዳደራቸው ባለሥልጣኖች ያሉባቸው ስምንት ሰዎች በፍንዳታው ተገድለዋል። ከንቲባው በፍንዳታው ቆስለው ኳታር ሲታከሙ ከቆዩ በኋላ ባለፈው ሳምንት ሃሙስ ማረፋቸው ይታወቃል።

በአሜሪካ ድምፅ ያለው የሶማልኛ አገልግሎት በዘገበው መሰረት ሁለቱ ሴቶች፣ በከተማይቱ አስተዳደር ለመቀጠር ሲሉ የሃሰት ስም ነበር የተጠቀሙት።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG