ዋሺንግተን ዲሲ —
የታች ሸበሌ ክልል ምክትል ገዥ አብዲፈታህ ሃጂ አብደላ ለአሜሪካ ድምፅ ሶማልኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል መሠረት፣ ወተት የጫነ ተሽከርካሪ በተቀበረ ፈንጂ ላይ በመሄዱ፤ ውስጡ የነበሩት ስምንቱም እንዳለ ሞተዋል።
የሞቱት ሦስት ወንዶችና አምስት ሴቶች በቀንድ ከብት አርቢ የሚተዳደሩ ሲሆኑ፣ ከአፍጎዬ 6 እና 7 ኪሜ ወጣ ብላ በምትገኘው ዶንካ ይኖሩ የነበሩት እነዚሁ ሰለባዎች፣ የክልሉ ምክትል ገዥ እንዳስረዱት፣ ወተት ከመኖሪያቸው ዋንላውይን ወደ ሞቅዲሾ ሲያጓጉዙ ነበር አደጋው የደረሰባቸው።
ባለሥልጣናት በሰጡት ቃል፣ ቀደም ባለውና 17 ሰዎች ሞተው ሌሎች 44 ለቆሰሉበት ጥቃት አል-ሻባብ ተጠያቂ ነኝ ማለቱን አስታውሰው፣ ይኸኛውንም፣ “ከእርሱ ራስ አይወርድም” ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ