በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ህብረትና የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች አዲስ አበባ ናቸው


ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲና ሙፍቲ
ፎቶ ፋይል፦ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ የሚገኙት የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆና የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈሪ ፌልትማን አዲስ አበባ ናቸው።

የፌልትማንን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ልዩ መልዕክተኛው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረት ተወካዮች እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ግጭቱን ለማስቆም በድርድር ዘላቂ ተኩስ አቁም ማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚነጋገሩ አስታውቋል።

በሌላ በኩልም የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ አዲስ አበባ መግባታቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆና የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፈሪ ፌልትማን ዛሬ ወደ አዲስ አበባ የገቡት በኢትዮጵያ አንድ ዓመት ያስቆጠረው ግጭት አብቅቶ የሰላም ሥምምነት እንዲካሄድ ጥረት ሊያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲና ሙፍቲ መናገራቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

“ሁለቱም ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ መንግሥት እና አማፂው የህወሃት ታጣቂዎች እና አጋሮቻቸው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ እንዲያቆሙ እና በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነቱ ለተጎዱ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ” የሚሉ ጥያቄዎች ማቅርባቸው ተዘግቧል።

በሌላ ዜና በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ምክንያት ችግር እንደደረሰባቸው በዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሠሩ አንዳንድ የውጭ አገር ዜጎች ቅሬታ እንዳቀረቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለፁ።

ሕጉ ዜግነት ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነም ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። አንዳንድ ግዙፍ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት አሁንም ከሃገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጋጩ ዘገባዎችን ያቀርባሉ ሲሉም ቃል አቀባዩ ነቅፈዋል።

ቃል አቀባዩ የሰጡትን መግለጫ ዝርዝር ጉዳይ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ​።

የአፍሪካ ህብረትና የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች አዲስ አበባ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00


XS
SM
MD
LG