በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ግድቡና ምርጫው የኢትዮጵያን ገፅታ ይቀይራሉ” - ዲና ሙፍቲ


የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ፣ የሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ሙሌት እና ወቅታዊው የትግራይ ክልል ጉዳይ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ምህዳር እና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ እይታ በመቀየር ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ ከምርጫው እና ከግድቡ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ ይከሰታሉ ተብለው የተጠበቁ መዘዞች አለመከሰታቸው ለፖለቲካው ምህዳር መቀየር ምክንያት እንደሆኑ ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ካለው ሁኔታም ጋር በተያያዘ ነገሮች በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከሚጠበቁት በተቃራኒው መሆናቸውን ነው አምባሳደር ዲና የተናገሩት፡፡

ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ ከአውሮፓ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ጋር በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት፣ ሕብረቱ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ከመፍጠር እንዲቆጠብ መግለጻቸውንም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ( በተለይም ምዕራባውያን ሀገራት) በኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና እየፈጠሩ ስለመሆናቸው የኢትዮጵያ መንግስት በተደጋጋ መግለጹ ይታወሳል፡፡

ከሕዳሴ ግድቡ ጋር በተያያዘ፣ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለሚደረገው ድርድር የኮንጎን ግብዣ በመጠባበቅ ላይ መሆኗን ገልጸው ይሁንና ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚባል ስምምነት ፈጽሞ እንደማትቀበል ጠቁመዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ግድቡና ምርጫው የኢትዮጵያን ገፅታ ይቀይራሉ” - ዲና ሙፍቲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:56 0:00


XS
SM
MD
LG