በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞደርና "የኮቪድ ክትባቶችን ለደሆች ሀገሮች አያቀርብም" ኒው ዮርክ ታይምስ


ሞደርና ኩባኒያ ኮቪድ አስራ ዘጠኝን "ከየትኛውም ክትባት ይበልጥ የሚከላከል ተደርጎ የሚወስደውን ክትባቱን በሙሉ በሚያሰኝ ደረጃ በሚያሰኝ ደረጃ የሚያቀርበው ለባለጸጎቹ ሃገሮች ነው" ሲል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገበ።

ሞደርና ደሆቹን ሃገሮች እያስጠበቀ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ይሰበስባል ሲል የኒው ዮርክ ታይምሱ ሪፖርት አመልክቷል።

ኒው ዮርክ ታይምስ ለሪፖርቱ መሰረት ያደረገው በዐለም ዙሪያ የሚላኩ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ክትባቶችን ከሚከታተለው ኤየርፊኒቲ ከተባለው የመረጃ አጠናቃሪ ድርጅት ያገኘውን አሃዛዊ መረጃ መሆኑ አስታውቋል።

በኒው ዮርክ ታይምሱ ሪፖርት መሰረት ሞደርና ካመረተው የኮቪድ ክትባት ውስጥ ለደሃ ሃገሮች የላከው አንድ ሚሊዮን ነጠላ ክትባት ብቻ ነው። በንፅፅር ፋይዘር ስምንት ነጥብ አራት ሚሊዮን፥ ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ደግሞ ሃያ አምስት ሚሊዮን ክትባቶችን እንደላኩ ሪፖርቱ አውስቷል።

ከዚህም ሌላ የአንዳንድ ባለመካከለኛ ገቢ ሃገሮች ባለስልጣናት የሞደርናን ክትባት ለመግዛት ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ህብረት ከከፈሉት የሚበልጥ ገንዘብ ከፍለናል ማለታቸውን የኒው ዮርክ ታይምሱ ዘገባ አመልክቷዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ጣሊያን ዋና ከተማ ሮም ላይ እ አ አ ከመጪውጥቅምት 15 ጀምሮ በሀገሪቱ ተግባራዊ የሚሆነውን የመንግሥት እና የግል ዘርፍ ሰራተኞች የክትባት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ግዴታ በመቃወም በብዙ ሺዎች የተቆጠሩ ሰዎች ሰልፍ አካሂደዋል።

የወጣውን ደንብ የማያከብሩ ሰራተኞች እና አሰሪዎች ቅጣት ይጣልባቸዋል ተብሏል። የመንግስት ሰራተኞች መከተባቸውን ወይም በቀደሙት አርባ ስምንት ሰዐታት ውስጥ ተመርምረው ቫይረሱ እንደሌለባቸው ማረጋገጫ ሳይይዙ አምስት ጊዜ ስራ ቦታቸው ሄደው ከተገኙ ከስራ እንደሚታገዱ ተደንግጓል።

በዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ የኮቪድ ክትባት ያልተከተቡ አንድ የፖለቲካ ሰው ለኮሮና ቫይረስ መጋለጣቸውን እና ሞኖክሎናል የሚባለውን የሰውነት የተፈጥሮ መከላከያ መቀስቀሻ መርፌ እየተወጉ ህክምና ላይ መሆናቸውን ተናገሩ። ለቴክሳስ አገረ ገዢነት በሪፐብሊካን ፓርቲው ዕጩነት ለመወዳደር የሚፈልጉት አለን ዌስት እሳቸው የኮቪድ ክትባት እንዳልተከተቡ ገልጸዋል። ባለቤታቸው ግን ክትባቱን መውሰዳቸውን ሆኖም ቫይረሱ እንደያዛቸው አመልክተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የኮቪድ መረጃ ማዕከል መሰረት በዐለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ237 ሚሊዮን አልፏል። በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን ያጡት ቁጥርም ወደአምስት ሚሊዮን እየተቃረበ ነው።

XS
SM
MD
LG