በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአህያ የሚጐተት ቤተ መፃህፍት በመቀሌ


የEthiopia Reads /ኢትዮጵያ ታነባለች/ መስራችና ስራ አስከያጅ አቶ ዮሃንስ ገ/ጊዮርጊስ በመቀሌ የመጀመሪያው በአህያ የሚጐተት ቤተ መፃህፍት አስጀመሩ፡፡

በተጨማሪም እሁድ ነሐሴ 16 የመጀመሪያው የህፃናትና የወጣቶች ቤተመፃህፍት ተከፍቶ የነፃ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ቤተ መፃህፍቱ ሰገናት ቤተ መፃህፍት ተሰይሟል፡፡

“የመቀሌ መስተዳድር ለቤተ መፃህፍቱ የሚሆን ቤት በነፃ በመስጠት ባይተባበረን ቤተ መፃህፍቱ ባልተከፈተ ነበር” ሲሉ አቶ ዮሃንስ ለመስተዳደሩ በተለይ ደግሞ ለመቀሌ ከንቲባ አቶ ፍስሃ ዘሪሁን ያላቸውን ታላቅ ክብርና ምስጋና ያቀርባሉ፡፡

ነሐሴ 16 የሚከበረው አሸንዳ የትግራይ ልጃገረዶች በአልን ምክንያት በማድረግም በአቶ ዮሃንስ የተዘጋጀ “አሸንዳ” የሚል ስለ በዓሉ የሚተርክ መፃህፍም ታትሞ ለ5000 ልጃገረዶች በነፃ ታድሏል፡፡

የህፃናትና የወጣቶችን እንዲሁም የህብረተሰቡ የንባብ ባህል ለማሳደግ ደግሞ በአህያ የሚጐተት ተንቀሳቃሽ ቤተ መፃህፍት እንደ ጥሩ ኣማራጭነት ቀርቧል፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG