በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማርቲን ሉተርኪንግ ቀን ዛሬ ተከበረ!


".. ሕልም አለኝ! አራቱ ትንንሽ ልጆቼ አንድ ቀን በቆዳቸው ቀለም ሳይሆን፤ በምግባራቸው የሚለኩባት አገር ውስጥ እንደሚኖሩ .. ዛሬ ሕልም አለኝ! .." ማርቲን ሉተር ኪንግ - እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ነሃሴ 28, 1963 ዋሽንግተን ዲሲ።

ጥቁር አሜሪካዊው የመብት ተሟጋች ማርቲን ሉተር ኪንግ በነፍሰ-ገዳይ ጥይት ከተገደሉ ዛሬ 51 ዓመት ሞላቸው።

በአውሮፓውያን የዘመን ቆጠራ ስሌት እንዲህ እንደ ዛሬው በያመቱ የጥር ወር በገባ ሦሥተኛው ሰኞ (የልደት ቀናቸውን ጥር 15’ን አስታኮ) በሚከበረው የመታሰቢያ ቀናቸው የጥቁር አሜሪካዊውን ሰባኪ፤ የእኚህን ታላቅ የመብት ተሟጋች ሕይወትና ሥራ በሚዘከር ቅንብር አንድ እንግዳ ጋብዘናል።

አቶ ቴዎድሮስ አበበ በሞያቸው እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ ሲኒየር አርካይቪስት ሲሆኑ፤ በስነ-ግጥምና ታሪክ ነክ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ በሚያተኩሩ ጽሁፎቻቸው ይታወቃሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የማርቲን ሉተርኪንግ ቀን ዛሬ ተከበረ!
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:59 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG