ዋሽንግተን ዲሲ —
በዩናይትድ ስቴትስ የቀን መቁጠሪያ ላይ በፌደራል በዓላቱ ዝርዝር ውስጥ ሥራ ዝግ ሆኖ በግለሰብ ስም ክብር የሚደረግባቸው ቀኖች ሁለት ብቻ ናቸው። አንድም ለሃገሪቱ መሥራች አባት ጆርጅ ዋሺንግተን፤ አንድም ለሲቪል መብቶች ትግል አውራው ማርቲን ሉተር ኪንግ።
የጆርጅ ዋሺንግተንም የልደት ቀን ቢሆን በአብዛኛው “የፕሬዚዳንቶች ቀን” ተብሎ ነው የሚታወቅ። የዛሬው ዕለት ግን ኤምኤልኬ ዴይ፣ ኪንግ ዴይ፣ ቄስ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ቀንም እየተባለ በስማቸው ይጠራል።
ኪንግ የተወለዱት ጥር 7/1921 ዓ.ም. ነው /በኢት. አቆጣጠር/ በለጋ ዕድሜያቸው ባይቀጩ ዛሬ የ93 ዓመት አዛውንት ነበሩ።
ዕለቱ መታሰቢያ በሆነላቸው የሲቪል መብቶች ትግል ዓመታት ላይ ቀደም ሲል በቪኦኤ ተዘጋጅተው ከነበሩ የታሪክ ትውስታዎች አንድ ሁለቱን እናሰማችሁ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያገኛሉ።