በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማርቲን ሉተር ኪንግ ቀን


የጥቁሮች መብት ታጋይ እና የነጻነት አቀንቃኝ ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ
የጥቁሮች መብት ታጋይ እና የነጻነት አቀንቃኝ ማርቲን ሉተር ኪንግ መታሰቢያ

ዩናይትድ ስቴትስ እ.ኤ.አ 1986 ዓ.ም ጀምሮ የጥቁሮች መብት ታጋይ እና የነጻነት አቀንቃኝ ማርቲን ሉተር ኪንግን የልደት መታሰቢያ እኤአ ጥር 17 ስታከብር የቆየች ስትሆን በዛሬውም ዕለት ይህንኑ በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የቀን መቁጠሪያ ላይ በፌዴራል በዓላቱ ዝርዝር ውስጥ ሥራ ዝግ ሆኖ በግለሰብ ስም ክብር የሚደረግባቸው ቀኖች የሃገሪቱ መሥራች ናቸው የሚባሉት ጆርጅ ዋሺንግተን፤ አንድም ለሲቪል መብቶች ትግል አውራው ማርቲን ሉተር ኪንግ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ይሁን እንጂ የዘንድሮ መታሰቢያ በዓል የሚታሰበው የነጻነት አቀንቃኙ ማርቲን ሉተር ኪንግ ይታገሉላቸው ከነበሩት ነገሮች አንዱ የሆነው በተለይም የጥቁር መራጮች መብት አከራካሪ በሆነበት ሁኔታ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዘንድሮው የልደት በዓል ለህግ መወሰኛ ምክር ቤት የቀረበው የመራጮች መብት ሕግ ባለመጽደቁ ምክንያት የጥቁሮች መብት በዘመናት ምንም ያህል አለተራመደም በሚል ከባድ ወቀሳ ውስጥ የሚከበር መሆኑም ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG