በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የመገበያያ ገንዘብ


የደቡብ ሱዳን መንግሥት በሃገሪቱ የሚደረገው የገንዘብ ልውውጥ ሁሉ በአሜሪካ ዶላር መሆኑ ቀርቶ፣ በሀገሪቱ ገንዘብ ፓውንድ እንዲሆን ማዘዙን፣ የሚቃወሙና የሚደግፉ እንዳሉ ተዘግቧል።

በመዲናይቱ ጁባ ያሉት የንግድ መሪዎች፣ አዲሱ ህግ የንግድ ሥራቸውን፣ አደጋ ላይ እንደሚጥል ገልጸዋል።

የሀገሪቱ የማስታወቅያ ሚኒስትር ማይክል ማኩየይ ባለፈው ሳምንት ለጋዜጠኞች በተናገሩት መሰረት፣ ፕሬዚዳንት ሳላቫ ኪር በሃገሪቱ ስላልለው የኢኮኖሚ ቀውስ፣ መፍትሄ ለማገኘት ሲሉ፣ ከአንድ ወር በፊት የመደቡት ኮሚቴ፣ 34 እርምጃዎች እንዲወሰዱ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል። ከቀረቡር ምክረ-ሃሳቦች አንዱም፣ በሃገሪቱ የሚካሄዱት የንግድ ሥራዎች ሁሉ፣ በሃገሪቱ ገንዘብ እንዲገለገሉ እንደሚጠይቅ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

“ደቡብ ሱዳን ውስጥ ማንኛውም ኮንትራት፣ የቤትና የመኪና ኪራይ ሳይቀር የሚደረገው በዶላር ነው። ብሄራዊ ገንዘብ እያላን ለምንድነው የውጭ ገንዘብ የምንጠቀመው?” ብለዋል የማስታወቂያ ሚኒስትሩ።

XS
SM
MD
LG