በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግብርና ሚኒስቴር 'ድርቅ እንጂ ረሃብ የለም' አለ


በኢትዮጵያ አሁንም ሆነ ባለፉት ሃያ ዓመታት ድርቅ እንጂ ረሃብ የለም ሲል የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት የኢትዮጵያ የግብርና ሚኒስትር ደኤታ ምትኩ ካሣ በድርቁ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥርም የፊታችን ጥቅምትና ኅዳር በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ አስታውቀዋል፡፡

አቶ ምትኩ ካሣ በኢትዮጵያ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር የአደጋ መከላከል፣ ዝግጁነትና የምግብ ዋስትና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ናቸው፡፡ የአሜሪካ ድምፁ ዘጋቢ እስክንድር ፍሬው ሰሞኑን ለችግሩ ማሣያ ይሆኑ ዘንድ የተመለከትኳቸውን የድርቅ ወረዳዎች መገሻ ያደረጉ ጥያቄዎችን አቅርቦላቸዋል፡፡

በአንዳንድ ወረዳዎች የተረጂው ቁጥር መጨመሩ ታይቷል፡፡ በሃገር አቀፍ ደረጃስ? አቶ ምትኩ ያብራራሉ፤

ዝርዝሩን ቃለምልልሱን ከያዘው ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG