በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ሴንት ሉዊስ ከተማ ት/ቤት ሦስት ሰዎች ተገደሉ


ሴንት ሉዊስ ፖሊስ
ሴንት ሉዊስ ፖሊስ

በዩናይትድ ስቴትስ መካከለኛው ምዕራብ ክፍለ ግዛት ሚዙሪ ሴንት ሉዊስ ከተማ በሚገኝ አጠቃላይ ትምህር ቤት ውስጥ ዛሬ ጧት በተከሰተ የተኩስ ጥቃት ተጠርጣሪ አጥቂውን ጨምሮ ሦስት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ፡፡

የሴንት ሉዊስ ፖሊስ ኮሚሽነር ማይክል ሳክ፣ በጥቃቱ ሌሎች ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸው አንዲት አዋቂ ሴት አንዲት ልጃገረድና ተጠርጣሪው ራሱ መሞታቸውን አስታውቀዋል፡፡

ብዙዎቹ ተማሪዎች በትምህርት ክፍላቸው ውስጥ ተደብቀው መቆየታቸውን ሴንት ሉዊስ ፖስት ዲስፓች ለተባለ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡

ከጧቱ ሶስት ሰዐት አካባቢ ሲሆን የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር በድምጽ ማጉያ “ጥቃት የሚያደርስ ሰው ትምህርት ቤቱ ግቢ ውስጥ ገብቷል” ብለው በምስጢራዊ መንገድ (ኮድ) መናገራቸውን የሂሳብ መምህሩ ዴቪድ ዊሊያም ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡

የተጠርጣሪው አጥቂ ማንነት ያልተለየ ሲሆን ፖሊስ 20 ዓመት ገደማ የሚሆነው ሰው ነው ማለቱን አሶሲየትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG