በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በሦሪያ ጉዳይ


የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ

"የሩሲያ ኃይሎች ወደ ሦሪያ የሚተኮሱ ማናችውንም ሚሳይሎች አየር ላይ ቀልበው ይጥላሉ" ሲሉ በሊባኖስ የሩሲያ አምባሳደር ከተናገሩ በኋላ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ መልስ ሰጥተዋል።

"የሩሲያ ኃይሎች ወደ ሦሪያ የሚተኮሱ ማናችውንም ሚሳይሎች አየር ላይ ቀልበው ይጥላሉ" ሲሉ በሊባኖስ የሩሲያ አምባሳደር ከተናገሩ በኋላ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ መልስ ሰጥተዋል።

“ሚሳይሎቹ እየመጡ ስለሆነ ሩሲያ መዘጋጀት አለባት” ብለዋል ፕሬዚዳንት ትረምፕ።

ሚስተር ትረምፕ በዛሬው የትዊተር መልዕክታቸው “በመርዝ ጋዝ የራሡን ዜጎች መፍጀት ከሚያስደስተው አውሬ ጋር ሸሪክ መሆን አያስፈልግም” ብለዋል።

ሞስኮ በሰጠችው ምላሽ “የዩናይትድ ስቴትስ ሚሳይሎች ዒላማ ማድረግ ያለባቸው አሸባሪዎችን እንጂ በሦሪያ ያለውን ሕጋዊ መንግሥት አይደለም ብላለች።

የክሬምሊኑ ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፖስኮቨ አክለውም በሩሲያው ጦርነት የሚሳተፉ ሁሉ አካባቢውን ከሚያናጋ ማናቸውም እርምጃ መታቀብ አለባቸው ብለዋል።

የሦሪያ መንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን በበኩሉ

“የዩናይትድ ስቴትስ የሚሳይል ዛቻ አላስፈላጊና ሁኔታዎችን የሚያባብስ ካልሆነ በቀር መፍትሄ አይሆንም” ብሏል።

በሦሪያ ባለፈው ቅዳሜ ጉታ ውስጥ ኬሚካላዊ የጦር መሣሪያ ጥቃት በትንሹ አርባ ሰዎችን ከገደለ በኋላ ሁኔታው በእጅጉ ተባብሷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG