በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አትሌት ምሩፅ ይፍጠር በ72 ዓመት ዕድሜው አረፈ


በአትሌቲክሱ የረዥም ርቀት ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያን በበርካታ ዓለምቀፍ መድረኮች በበላይነት ያስጠራው ዝነኛው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር በ72 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

አትሌት ምሩፅ ይፍጠር የአርባ ዓመት ጎልማሳ በነበረበት ወቅት ነው ሁለት የወርቅ መዳሊያዎችን በ1980 የሞስኮ ኦሎፒክ ላይ ያስገኘው፡፡ በ1972 ሙዩኒክ ኦሎፒክም የነሃስ መዳሊያ ተሸልሟል፡፡

በቅፅል ሰሙ “ማርሽ ቀያያሪው ሯጭ” በመባል ይጠራ የነበረው ምሩፅ ይፍጠር በስደት ይኖርበት ከነበረው ካናዳ ለብዙ ጊዜ ታሞ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

“ለእኔ እና ለኢትዮጵያ አትሌቶች ምሩፅ ዋነኛ አነቃቂያችን ነው” ያለው ታዋቂው ሯጭ ኃይሌ ገብረሥላሴ “ለእኔ ከዚህ መድረስ ምክንያት ነው” ሲልም አወድሶታል፡፡ ወንድ ልጁ ቢንያም ምሩፅ በበኩሉ ሲናገር አባቱ ለረጅም ጊዜ የመተንፈስ ችግር እንደነበረበት አስረድቷል፡፡

ምሩፅ ይፍጠር የሰባት ልጆች አባት ነበር፡፡

XS
SM
MD
LG