በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ተወሰነ። የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ዛሬ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ፣ ከዚህ በፊት በተወሰነው የመቁረጫ ነጥብ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከሚገቡት ተማሪዎች ውጭ ግጭት አለባቸው ከተባሉ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች እንደሚገቡ አስታውቋል፡፡ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚኒስቴሩን እርምጃ አድንቀዋል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጁን 03, 2023
ባንተኛስ?!
-
ጁን 02, 2023
በመስጂዶች ማፍረስ በቀጠለው ተቃውሞ የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ
-
ጁን 02, 2023
የዕውቀት አሸጋጋሪው - “ቤማንዳ” የምስጋና ምሽት
-
ጁን 02, 2023
በካሜሩን ባህላዊ መሪው ከ18 ወራት እገታ በኋላ ተለቀቁ
-
ጁን 02, 2023
የ“ሲድ ኢትዮጵያ”- የዘንድሮ ተሸላሚ ብርቱ ኢትዮጵያውያን