በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዐማራ ክልል የተመደቡ ፈታኝ መምህራን ለልመና እንደወጡ ሲያማርሩ ትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ በቅርቡ እንደሚያስወጣቸው ገለጸ

በዐማራ ክልል የተመደቡ ፈታኝ መምህራን ለልመና እንደወጡ ሲያማርሩ ትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ በቅርቡ እንደሚያስወጣቸው ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:00 0:00

በዐማራ ክልል የተመደቡ ፈታኝ መምህራን ለልመና እንደወጡ ሲያማርሩ ትምህርት ሚኒስቴር ደግሞ በቅርቡ እንደሚያስወጣቸው ገለጸ

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት፣ በዐማራ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ መምህራን፣ ወደየአካባቢያቸው መመለስ ባለመቻላቸው ለችግር እንደተዳረጉ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ፡፡

በጎንደር እና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውን የተናገሩ ፈታኝ መምህራን፣ የተሰጣቸውን አበል እንደጨረሱና የዕለት ምግብም ለማግኘት እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡ መንግሥት በአፋጣኝ ካሉበት አውጥቶ ወደመጡበት እንዲመልሳቸውም ተማፅነዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ፣ መምህራኑን ካሉበት አውጥቶ ወደ መጡበት ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ለአሜሪካ ድምፅ መረጃ የሰጡት፣ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዲሬክተር ዶር. እሸቱ ከበደ፣ በዐማራ ክልል የተመደቡትን መምህራን፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በቻርተርድ አውሮፕላን ለማስወጣት፣ የሚመለከተውን አካል ፈቃድ እየተጠባበቁ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG