አዲስ አበባ —
ፈተናው ለተማሪዎች ከመሰጠቱ በፊት ተሰርቆ ስለመውጣቱ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቁ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን መንግሥትም ከተለያዩ አካላት መረጃዎች እንደደረሱት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ገልጸዋል፡፡
ጉዳዩን በማጣራት እርምጃ እንደሚወስድም አቶ ተፈራ ገልፀዋል፡፡ አሁን ላይ ፈተናውን የተፈተኑ ተማሪዎች የውጤት ምዘናና የዩኒቨርሲቲ ምደባ፣ በጸጥታ ምክንያት ያልተፈተኑ ቀሪ ተማሪዎች ከተፈተኑ በኋላ በጋራ እንደሚገለጽም ምክትል ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡