በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምዕራብ አፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እጦት ይገጥማቸዋል - የተመድ


ፎቶ ፋይል፦ ዮላ፣ ናይጄሪያ፣ 8/22/2016
ፎቶ ፋይል፦ ዮላ፣ ናይጄሪያ፣ 8/22/2016

በምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ 45 ሚሊዮን የሚሆኑ ሠዎች ላለፉት 10 ዓመታት ባልታየ ሁኔታ በሚቀጥሉት ወራት የምግብ ዋስትና ችግር ይገጥማቸዋል ሲል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል፡፡

ችግሩ የተባባሰውም በጸጥታ አለመኖር፣ በአየር ንብረት ለውጥ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ እና በምግብ ዋጋ መናር ምክንያት መሆኑን የተመድ የሰብዓዊ ወኪል ድርጅቶች አስታውቀዋል፡፡

በምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ በተዛባ ዝናብና ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የምግብ እጥረት እንደገጠማቸውና፣ በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነትም የምግብና የማዳበሪያ እጥረት እንዳስከተከለ ታውቋል፡፡

ከሰኔ እስከ ነሐሴ ባለው ግዜ ውስጥ የምግብ እጥረቱ 48 ሚሊዮን ሰዎችን ሊነካ እንደሚችል የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማተባበሪያ ቢሮው ኦቻ፣ የምግብና የእርሻ ድርጅቱ ፋኦ እንዲሁም የሕጻናት አድን ድርጅት ዩኒሴፍ አስታውቀዋል፡፡

በሳህል የሚገኙ 45 ሚሊዮን ሰዎች ከፍተኛ የምግብ ዕጥረት እንደሚገጥማቸውም ድርጅትቶቹ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

XS
SM
MD
LG