በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት የምዕራብ አፍሪካ ወታደራዊ መሪዎች የፀጥታ ስምምነት ተፈራረሙ


የቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ካርታ
የቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ካርታ

የቡርኪናፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር ወታደራዊ አመራሮች ባለፈው ሳምንት መጨረሻ፣ የጋራ መከላከያ ስምምነት ተፈራርመዋል። ሦስቱ የጁንታ መሪዎች 'ሊፕታኮ-ጉርማ' የተሰኘውን ቻርተር የተፈራረሙት የሳህል ግዛቶች ጥምረትን በማቋቋም ነው። ስምምነቱ ስያሜውን ያገኘው፣ የሦስቱ ሀገራት ድንበሮች ከሚገናኑበት አዋሳኝ ክልል ነው።

ስምምነቱን ተከትሎ የማሊ ወታደራዊ መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ባወጡት መግለጫ፣ "ከቡርኪናፋሶ እና ኒጀር መሪዎች ጋር የሳህል ቀጠና ሀገራትን ጥምረት በመመስረት 'ሊፕታኮ-ጉርማ' ቻርተርን የፈረምነው፣ ለሁሉም ሕዝቦች የጋራ ጥቅም የሚሆን መከላከያ ርዳታ ለማቋቋም ነው" ብለዋል።

ሦስቱ ጎረቤት ሀገራት ከአክራሪ ሽብርተኞች የጥቃት ስጋት ያለባቸው ሲሆን፣ አዲሱ የጋራ ስምምነት፣ አንዳቸው አንዳቸውን ከጥቃት ለመጠበቅ የሚያስችላቸው ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG