በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ወታደራዊ ፍርድቤት ስድስት የሞሮኮ ተወላጆች ላይ ሞት ፈረደ


አንድ ኢትዮጵያዊ የ10 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈርዶበታል

በሶማሊያ ሰሜናዊ ምስራቅ ከፊል ራስ ገዝ በሆነው ፑንትላንድ የሚገኝ ወታደራዊ ፍርድ ቤት፣ የፅንፈኛው እስላማዊ መንግሥት ቡድን የውጭ ተዋጊ ናቸው ባላቸው ስድስት የሞሮኮ ተወላጆች ላይ ሞት ፈረደ።

ግለሰቦቹ ወደ ሶማሊያ የገቡት በሙስሊሞች እና በሶማሌዎች ላይ ጉዳት ለማድረስ እና በሀገሪቱ ብጥብጥ ለመፍጠር ነው ሲሉ በፑንትላንድ ግዛት በሚገኘው ፍርድቤት ሰብሳቢ ዳኛ አሊ ኢብራሂም ኦስማን ባለፈው ሐሙስ ተናግረዋል።

ስማቸው ሞሐመድ ሀሰን፣ አህመድ ናጃዊ፣ ካሊድ ላታ፣ ሞሐመድ ቢኑ ሞሐመድ አህመድ፣ ሪድዋን አብዱልቃድር ኦስማኒ እና አህመድ ሁሴን ኢብራሂም መሆናቸው የተገለፀው ስድስቱ ሰዎች ይግባኝ ማለት የሚችሉ ሲሆን፣ የይግባኝ ጥያቄያቸው ተቀባይነት ካላገኘ በጥይት ይገደላሉ።

ከስድስቱ በተጨማሪ አንድ ኢትዮጵያዊ እና አንድ ሶማሊያዊ እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ተፈርዶባቸዋል። ሌላ ሶማሊያዊ ተከሳሽ ደግሞ ማስረጃ ስላልቀረበበት በነፃ ተሰናብቷል።

ተከሳሾቹ የሕግ ውክልና ማግኘት መቻላቸው ያልተገለፀ ሲሆን የት እንደታሰሩም አልታወቀም።

ስምንቱ ሰዎች ፅንፈኛውን ቡድን የተቀላቀሉት በስህተት መሆኑን ተናግረው ወደ ሀገራቸው የመመለስ ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውንም ድኛው ኦስማን አስረድተዋል።

ኦስማን አክለው ስድስቱ ሞሮካዊያን የቡድኑ ጠንካራ ምሽግ ሆኖ በሚያገለግለው እና በሰሜትን ምስራቅ ሶማሊያ በሚገኘው ካል-ሚስካት ተራሮች ከእስላማዊ መንግስት ጋር ስልጠና መሰደዳቸውን ገልፀዋል።

ስድስቱም የተያዙት የፑንትላንድ ግዛት የንግድ ማዕከል ከሆነው ቦሳሶ በስተምስራቅ በሚገኝ ተራራማ አካባቢ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG