በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወታደራዊ ትንታኔ፦ በትግራይ እየተካሄደ ያለው ውጊያ


በኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት እና በህወሓት በሚመራው የክልሉ ኃይል መካከል በትግራይ በመካሄድ ላይ ያለው ውጊያ ቀጥሏል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በውጊያው በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠሩን፤ ትልሙን ለማስፈጸምም ወደፊት እየገፋ መሆኑን እና ከወታደራዊ ግጭቱ የመጨረሻ እርከን ላይ መድረሱን ይናገራል።

የኢትዮጵያ መንግስት “የሕግ ማስከበር ሥራ” ባለው በዚህ ወታደራዊ እርምጃ ሶስተኛ ምዕራፍ በሰባ ሁለት ሰዓታት እጃቸውን እንዲሰጡ ሲል “ለህወሓት አመራር ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። ህወሓት በበኩሉ ወደ መቀሌ የሚመጣውን ኃይል መክቶ ማስቆሙን ነው የተናገረው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በንጹሃን ዜጎች ላይ ሆን-ተብለው መፈጸማቸው የሚነገሩትን ጉዳቶች ጨምሮ በውጊያው ሳቢያ ለመፈናቀል እና ለበረታ ጉዳት የሚዳረጉ ዜጎች ጉዳይ፡ የግጭቱን ተጨባጭ መንሴዎችና የሁለቱን ወገኖች ለየቅል ዓላማ እና ግቦች፤ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጭብጦች በሁለቱ ወገኖች ከሚሰሙት መግለጫዎች አልፎ ለመመርመር የታለመ ውይይት ነው።

በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ያላቸውን ዕይታ ጨምረው ወታደራዊ ትንታኔውን የሰጡት በውጊያው በሁለቱም ወገን በቀጥታ ተሳታፊነት የሌላቸው ሦስት አንጋፋ የጦር መኮንኖች - ሜጀር ጀነራል መርዳሳ ሌሊሳ፤ ብርጋዴር ጀነራል አሰፋ አፈሮም እና ብርጋዴር ጀነራል መስፍን ኃይሌ ናቸው።

የውይይቱን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

ወታደራዊ ትንታኔ፡- ወታደራዊ ግጭት በትግራይ - ክፍል አንድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:22:18 0:00
ወታደራዊ ትንታኔ፡- ወታደራዊ ግጭት በትግራይ - ክፍል ሁለት
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:53 0:00


XS
SM
MD
LG