ዋሺንግተን ዲሲ —
ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሊዶ የባህር ዳርቻ በሚገኝ ሆቴል ትናንት ዕሁድ ምሽት በተፈፀመው እና አልሻባብ ኃላፊነት በወሰደበት ጥቃት ቢያንስ አሥራ አምስት ሰዎች ሲሞቱ፣ አስራ ስምንት ደግሞ ቆስለዋል።
የሶማሊያ ባለሥልጣናት እና እማኞች ለቪኦኤ የሶማሊኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል ትናንት ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ገደማ ላይ ኢሊት ሆቴል ደጃፍ ላይ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ የተጠመደበት መኪና ከፈነዳ በኋላ አራት ታጣቂዎች ሆቴሉን ጥሰው ገብተዋል።
ወዲያውኑ የፀጥታ ኃይሎች ደርሰው በተኩስ ልውውጥ አራቱን ታጣቂዎች የገደሏቸው መሆኑን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ለቪኦኤ ገልፀዋል። ወደሁለት መቶ የሚሆኑ የሆቴሉ እንግዶችና የሆቴሉን ባለቤት ሊያወጡ መቻላቸውንም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።