በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቱኒዚያ እና በምዕራብ ሰሃራ የባሕር ዳርቻ 16 ፍልሰተኞች ሞቱ


ፎቶ ፋይል፦ በዋነኛነት ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገሮች የፈለሱ በቱኒዚያ የባሕር ዳርቻ የሜድትሬንያን ባሕር አቋርጠው ወደ ጣሊያን በጀልባ ተጭነው ሲጓዙ እአአ ሚያዝያ 18 ቀን 2023
ፎቶ ፋይል፦ በዋነኛነት ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገሮች የፈለሱ በቱኒዚያ የባሕር ዳርቻ የሜድትሬንያን ባሕር አቋርጠው ወደ ጣሊያን በጀልባ ተጭነው ሲጓዙ እአአ ሚያዝያ 18 ቀን 2023

በቱኒዚያ የባሕር ዳርቻ በደረሰ የጀልባ አደጋ፣ 11 ፍልሰተኞች እንደሞቱ እና 44 የሚኾኑቱ ደግሞ የደረሱበት እንዳልታወቀ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ከሰሃራ በታች ከሚገኙ ሀገራት የመጡ ናቸው፤ የተባሉ 57 ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ፣ በሜድትሬንያን ባሕር ላይ መስመጡን ተከትሎ፣ የአደጋ ሠራተኞች ፍለጋ ላይ እንደተሰማሩ ታውቋል።

በተያያዘ ዜና፣ ከሴኔጋል የተነሡ 189 ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ፣ በምዕራብ ሰሃራ የባሕር ዳርቻ ተገልብጦ፣ አምስት ሰዎች እንደሞቱ፣ የሞሮኮ ባሕር ኃይል አስታውቋል። 11 ፍልሰተኞች ደግሞ፣ ለሕይወት በሚያሰጋ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ፣ ባሕር ኃይሉ አስታውቋል።

በሌላ በኩል፣ በደርዘን የሚቆጠሩ ፍልሰተኞችን እንደታደጉ፣ የጣልያን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። በላምፔዱሳ ደሴት አካባቢ፣ ለሁለት ቀናት መንቀሳቀስ ያልቻሉ 30 ፍልሰተኞችን፣ ትላንት እሑድ በሄሊኮፕተር መታደጋቸውን አስታውቀዋል።

ፍልሰተኞቹ፣ በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ጀልባ፣ ከቱኒዚያ መነሣታቸውን፣ ባለሥልጣናት ጨምረው አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG