በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎ አድራጎቱ 87 ፍልሰተኞችን ከባሕር ላይ ታደገ

በዓለም አቀፉ ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ንብረትነት የተያዘ መርከብ በአንዲት ከጎማ በተሰራች ጀልባ ላይ የነበሩ 87 ፍልሰተኞችን በሜዲትሬንያን  ባሕር ላይ ትላንት ከአደጋ መታደጉ ታውቋል።

‘ጂኦ ባረንትስ’ የተሰነችው መርከብ የታደገቻቸው ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ በማምራት ላይ ነበሩ።

የሊቢያ መንግስት መርከብ ወደ ጀልባዋ በመጠጋት ላይ ሳለ፣ ፍልክሰተኞቹ ለማምለጥ ወደ ባሕሩ ሲዘሉ የበጎ አድራጊ ድርጅቱ ሠራተኞች በቀረጹት ቪድዮ ላይ ታይቷል።

በጣልያን ሥራ ላይ በዋለ አዲስ ሕግ መሠረት፣ ፍልሰተኞችን የያዙ የበጎ አድራጎት መርከቦች ራቅ ብሎ ከሚገኝ ወደብ ላይ እንዲያራግፉ ይገደዳሉ። በዚህም ምክንያት አደጋ ላይ ያሉ ፍልሰተኖችን ከማዳንና መርዳት ይልቅ፣ በጉዞ ላይ ጊዜያቸውን እያባከኑ መሆኑን የረድኤት ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ናቸው።

በያዝነው የአውሮፓውያን ዓመት እስከ አሁን 884 ፍልሰተኞች በባሕር ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል። ከእነዚህ ውስጥም 48 የሚሆኑት ሕፃናት መሆናቸውን የተመድ ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ ኦ ኤም) አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG