በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማልታ ባህር ዳርቻ ከ400 በላይ ፍልሰተኞች ከአደጋ ተረፉ


ፎቶ ፋይል፡- ፍልሰተኞች በማልታ ከሚገኝ የባህሩ ዳርቻ አካባቢ
ፎቶ ፋይል፡- ፍልሰተኞች በማልታ ከሚገኝ የባህሩ ዳርቻ አካባቢ

በጎ አድራጊው ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን ከ400 በላይ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን ከማልታ ባህር ዳርቻ ላይ መታደጉን አስታወቀ፡፡

የቡድኑ መርከብ የድረሱልን ጥሪ ወዳሰሙት ፍልሰተኞች ለመድረስ በወጀብ በተናጠው ባህር ላይ ለ 10 ሰዓታት መጓዟ ታውቋል፡፡ በኋላም መርከቧ ፈጣን ጀልባዎችን ወደ ፍልሰተኞቹ በመላክ 8 ሴቶችንና 30 ሕጻናትን ጨምሮ 440 ፍልሰተኞችን ከአደጋ መታደጓን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል፡፡

ፍልሰተኞቹን የማዳን ሥራው 11 ሰዓታትን እንደወሰደም ታውቋል፡፡

“ጂኦ ባረንትስ” የተሰኘችው የድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን መርከብ ባለፈው የካቲት በሜዲትሬኒያን ባህር ላይ የሕይወት ማዳን ተግባር በምታከናውንበት ወቅት የመንግሥትን ሕግ ጥሳለች በሚል በጣሊያን ባለሥልጣናት ታግታ ቆይታ ነበር፡፡ መርከቢቱ የጉዞ መረጃዋን ለሚመለከተው ባለሥልጣን አልሳወቀችም የሚል ክስ እንደቀረበባቸው የሐኪሞቹ ቡድን አስታውቋል፡፡

የቀኝ ክንፍ ወግ አጥባቂ ፓርቲ መሪና የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የፍልሰተኞችን ቁጥር ለመቀነስ ቃል በመግባት ሥልጣኑን ይዘዋል፡፡ አዲስ ያወጡት ሕግ የበጎ አድራጊ መርከቦች በአንድ ወቅት አንድ የነፍስ አድን ሥራ ብቻ እንዲያከናውኑ ያዛል፡፡ ሕጉ የሞት አደጋን እንዲጨምር ያደርጋል ሲሉ ነቃፊዎች ይናገራሉ፡፡

የጣሊያን መንግሥት የነፍስ አድን መርከቦቹ ፍልሰተኞች እንዲበረታቱ አድርጓል ሲሉ ይከሳሉ፡፡

XS
SM
MD
LG