በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባህር ላይ ዘቦች 367 ፍልሰተኞችን ታደጉ


ፎቶ ፋይል፦ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገሮች የተነሱ፣ የአፍሪካ ስደተኞች ወደ ጣሊያን የባህር ዳርቻ ለመጓዝ ጀልባ ላይ ተቀምጠው።
ፎቶ ፋይል፦ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገሮች የተነሱ፣ የአፍሪካ ስደተኞች ወደ ጣሊያን የባህር ዳርቻ ለመጓዝ ጀልባ ላይ ተቀምጠው።

በትናንሽ ጀልባዎች ከፈረንሳይ ወደ እንግሊዝ በባህር ለማቋረጥ የሞከሩ ከ360 በላይ ፍልሰተኞችን የሃገሪቱ የባህር ላይ ዘብ እንደታደገ የፈረንሳይ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የአካባቢው የባህር ዘብ ጀልባዎችና የፈርንሳይ የባህር ኃይል በርካታ ጎዞዎችን በማድረግ በእንግሊዝ መተላለፊያ ቻነል ውስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ ፍልሰተኞችን አድነዋል ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል።

ፍልሰተኞቹ ካሌይ፣ ቡሎን፣ ደንክርክ ወደተባሉ የፈረንሳይ ወደቦች ተወስደዋል።

ወደ እንግሊዝ ለመግባት የሚሹ በርካታ ስደተኞች፣ እንደነገሩ በተሰሩ ጀልባዎች በመሆን የእንግሊዝ ቻነልን ለማቋረጥ ይሞክራሉ።

የእንግሊዝ ቻነል በዓለም ትራፊክ ከሚበዛባችው የመርከቦች መተላለፊያ አንዱ ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው በአብዛኛው አስቸጋሪ ነው። በቀን 400 የሚሆኑ መርከቦች በእንግሊዝ ቻነል ያልፋሉ።

ከያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ አንስቶ 35ሺህ 500 ሰዎች የእንግሊዝን ቻነል በጀልባ ተሻግረዋል።

ከእንግሊዝ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር በተገኘው መረጃ መሰረት፣ እንግሊዝ ከሚደርሱት ፍልሰተኞች ውስጥ 94 በመቶ የሚሆኑት ለጥገኝነት የሚያመለክቱ ሲሆን፣ አብዛኞቹ ለጥያቄያቸው በጎ ምላሽ ያገኛሉ።

XS
SM
MD
LG