በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍልሰተኞች የባሕር ላይ እልቂት እያሻቀበ ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ከሊብያ ወደ ጣልያን በሚወስደው የሜዲቴራኔያን ባሕር መሥመር ላይ የሚሞቱ ፍልሰተኞች ቁጥር ማሻቀቡን የሚያሳዩ ሪፖርቶች እየደረሱት መሆኑን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም አስታወቀ፡፡

ከሊብያ ወደ ጣልያን በሚወስደው የሜዲቴራኔያን ባሕር መሥመር ላይ የሚሞቱ ፍልሰተኞች ቁጥር ማሻቀቡን የሚያሳዩ ሪፖርቶች እየደረሱት መሆኑን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም አስታወቀ፡፡

አደጋው ጨምሮ የታየው በያዝነው የአውሮፓ ዓመት ያለፉ ሁለት የመጀመሪያ ወራት ነው፡፡

ባለፈው ዓመት በተመሣሣይ ጊዜ ሜዲቴራኔያን ባሕር ላይ የቀሩ ስደተኞችና ፍልሰተኞች ቁጥር 97 ብቻ ነበር፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ ጣልያን ለመድረስ ሊብያ ዳርቻ ላይ ወደ ባሕሩ እንደገቡ ሌላኛውን ዳርቻ ለማየት ያልታደሉት ቁጥር 326 ደርሷል፡፡

በዚያ ላይ ይህ ቁጥር እውነተኛውን የሰቀቀን መጠን አያሳይም፡፡ ያልተገኙ አስከሬኖች ቁጥር ብዙ ነው - የአይኦኤም ቃል አቀባይ እንደሚሉት፡፡

ከአደጋው ሰለባዎች አብዛኞቹ ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ ሃገሮች የተነሱ መሆናቸውን ቃል አቀባዩ ጆይል ሚላን ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

አፍሪካውያን ፍልሰተኞች
አፍሪካውያን ፍልሰተኞች

“ሊብያ ውስጥ እንደንግድ የተያዙ የጠለፋ አድራጎቶች ተሟሙቀዋል፡፡ ሰዎች ከየመንገዱ ታፍነው ይወሰዱና የማስለቀቂያ ክፍያ ከተወሰደባቸው በኋላ ወደ ጀልባዎቹ ተገፍተው እንዲገቡ ይደረጋሉ፡፡ ጠላፊዎቻቸው ክፍያዎቹን ከወሰዱ በኋላ ዘወር ብለው አያይዋቸውም፡፡ ሰዎቹ ወደየቤተሰቦቻቸው እየደወሉ እራሳቸውን ጥቂት የሚያቆዩበት ገንዘብ እንዲላክላቸው ወደመማፀን ይገባሉ፡፡ ስልክ የመደወሉ መንገድና አሠራር እራሱ እጅግ የተራዘመና አድካሚ ነው፡፡” ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡

“በእነዚህ እራሳቸውን የሚከላከሉበት አንዳች አቅም በሌላቸው ሰዎች ላይ የሚፈፀሙት እጅግ የከፉ ጥፋቶች” እየበዙ መምጣታቸውን የተናገሩት ሚላን ሕገወጦቹ አሸጋጋሪዎች ከጀልባዎቹ ላይ ሞተር እየሰረቁ እንደሚወስዱና በሰው የታጨቁትን ጀልባዎች ወደ ባሕሩ እንዲንሳፈፉ እንደሚለቅቋቸው ገልፀዋል፡፡

ነፍስ አድን መርከቦች መንገድ ላይ መሆናቸው ፍልሰተኞቹ በአሸጋጋሪዎቹ እንደሚነገራቸውና ብዙ ጊዜ የባሕር ላይ ፈጥኖ ደራሾች መንገደኞቹን ከያሉበት አደጋ ቢያወጧቸውም ጨርሶ ማንም የማይደርስላቸው ጊዜም ጥቂት አለመሆኑን ሚላን አመልክተዋል፡፡

የፍልሰተኞች የባሕር ላይ እልቂት እያሻቀበ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:26 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG