በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞች “በሊቢያ ድንበር ላይ እየተጣልን ነው” ሲሉ ቱኒዚያን ከሠሡ

ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገሮች የመጡ እና በቱኒዚያ የነበሩ በመቶ የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች፣ በሊቢያ ድንበር አቅራቢያ ወደሚገኘው በረሓ ተወስደው እንደተጣሉ ተናገሩ፡፡

በጸጥታ ሠራተኞች ታፍሰው ተጥለዋል፤ የተባሉት ፍልሰተኞቹ፣ በአደገኛ ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙም ተገልጿል፡፡

ከቱኒዚያ እና ሊቢያ አቅጣጫ በመጡ የሁለቱም ሀገራት ወታደሮች፣ ወዳልታወቀ የባሕር ዳርቻ እየተወሰዱ እንደኾነም፣ ፍልሰተኞቹ ተናግረዋል፡፡

በዚኽ ሳምንት፣ ሳፋክስ በተባለችው የቱኒዚያ ወደብ ከተማ፣ በነዋሪዎች እና በፍልሰተኞች መካከል ግጭት ከተነሣ እና አንድ ቱኒዚያዊ ዜጋ ከተገደለ በኋላ፣ ውጥረቱ እንደተባባሰ ተነግሯል፡፡

ከነዋሪዎች ሊነሣ ይችላል ያሉትን የበቀል ርምጃ የሸሹ፣ 200 የሚደርሱ ፍልሰተኞች፣ ወደ ቱኒዝያ ዋና ከተማ ቱኒስ፣ በባቡር አምልጠው እንደሔዱ ተዘግቧል፡፡

የተረፉትን ሌሎች ፍልሰተኞችንም ከጥቃት ለመከላከል፣ ፖሊስ ወደ መጠለያ ካምፕ እንዳስገባቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG