በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍልሰተኞችን የያዘ ጀልባ ከቋጥኝ ጋር ተጋጭቶ 59 ሞቱ

በደቡብ ጣሊያን ባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን የያዘ ከእንጨት የተሠራ ጀልባ ትናንት እሁድ ከቋጥኝ ጋር ተጋጭቶ 12 ሕጻንትን ጨምሮ ቢያንስ 59 መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

ወደ አውሮፓ ሲሻገሩ የነበሩትን ፍልሰተኞች የያዘው ጀልባ ፍርስራሽ በደቡብ ጣሊያን ባህር ዳርቻ ትናንት ሲንሳፈፍ ተገኝቷል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ የአንድ ወር ብቻ ዕድሜ ያለው ሕጻን ከአደጋው ከተረፉትና ቀድመው ከተገኙት መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡

ጀልባው ከአራት ቀናት በፊት ከቱርክ ተነስቶ እንደነበር የጣሊያን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጀልባው ከአፍጋኒስታንንና ኢራን የመጡትን ጨምሮ 200 ፍልሰተኞችን ይዞ እንደነበር ታውቋል፡፡

እስከ 30 የሚሆኑ ሰዎች አሁንም ሊገኙ እንዳልቻሉ የጣሊያን የአገር ውስጥ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የአውሮፓ ድንበር ጠባቂዎችና የጣሊያን ፖሊስ ጀልባዋን ከአንድ ቀን በፊት አይተዋት የነበረ ቢሆንም፣ ጠልፎ ወደ ዳር እንዲያወጣ የተላከው ቡድን ግን በአደገኛው ወጀብ ምክንያት ሙከራው ሳይሳካለት ተመልሷል፡፡

ወደ አውሮፓ መሻገር ለሚሞክሩ ፍልሰተኞ ጣሊያን የመግቢያ በር ነች፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የጠፉ ፍልሰተኞች ፕሮጀክት እንደሚለው ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 220 ፍልስተኞች በሜዲትሬኒያን ባህር ላይ ሕይወታቸውን አጥተዋል አልያም ጠፍተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG