በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ አውሮፓ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር ከስድስት ዓመት ወዲህ ከፍተኛው ነው


የአፍሪካ ፍልሰኞች በተጨናነቀ የጎማ ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር ወደ አውሮፓ ለማቋረጥ ከሊቢያ የባህር ዳርቻ አካባቢ በመድረስ የስፔን "አይታ ሜሪ" የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የእርዳታ ሰራተኞች መቅዘፊያ ጃኬት ሲሰጧቸው ይታያል፡፡
የአፍሪካ ፍልሰኞች በተጨናነቀ የጎማ ጀልባ በሜዲትራኒያን ባህር ወደ አውሮፓ ለማቋረጥ ከሊቢያ የባህር ዳርቻ አካባቢ በመድረስ የስፔን "አይታ ሜሪ" የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የእርዳታ ሰራተኞች መቅዘፊያ ጃኬት ሲሰጧቸው ይታያል፡፡

በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ ህብረት አገሮች ለመግባት ጥረት የሚያደርጉ ስደተኞች ቁጥር ባለፈው ዓመት 330 ሺህ መድረሱን የህብረቱ የድንበር እና የባህር ዳርቻዎች ጥበቃ ድርጅት ዛሬ አርብ አስታወቀ። ይህ አሃዝ ከ2016 ዓም ወዲህ ከፍተኛው መሆኑ ተነግሯል።

በተገባደደው የአውሮፓውያኑ 2022 ዓም ከተደረጉት ሙከራዎች ገሚስ ያህሉ በምእራብ የባልካን ክልል በየብስ የተደረጉ ናቸው ሲል ፍሮንቴክስ የተባለው የህብረቱ የድንበር እና የባህር ዳርቻዎች ጥበቃ ድርጅት የቅድመ ጥናት ስሌቶችን ዋቢ አድርጎ አመልክቷል።

ወደ አውሮፓ የሚገቡበት መንገድ ምንም ይሁን ምን ታዲያ ከአጠቃላዩ አሃዝ 47 በመቶ ያህሉን ድንበር አቋርጦ ለመግባት የተደረገ ሙከራ የፈጸሙት ሶሪያውያን፣ አፍጋኒስታውያን እና ቱኒዚያውያን ሆነው ተገኝተዋል። በተጨማሪም ከሙከራዎቹ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት ወንዶች መሆናቸውንም ፍሮንቴክስ ገልጧል።

እንደ አሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2015ዓም አብዛኞቹ በሃገራቸው ያለውን ግጭት ሸሽተው የተሰደዱ ሶሪያውያን የሆኑባቸው ቁጥራቸው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሃያ ሰባት አባል አገሮች ያሉትን የውሮፓ አህጉር ያጥለቀለቀ የፖለቲካ ቀውስ መቀስቀሳቸው አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG