በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሄዝቦላ ከ50 በላይ ተጨማሪ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አስወነጨፈ


የሌባኖሱ ሄዝቦላ ከሃምሳ የሚበልጡ ሮኬቶችን ዛሬ ወደ እስራኤል ያስወነጨፈ ሲሆን ጎላን ሃይትስ በሚገኙ በርካታ የግል መኖሪያ ቤቶችን አፍርሷል።
የሌባኖሱ ሄዝቦላ ከሃምሳ የሚበልጡ ሮኬቶችን ዛሬ ወደ እስራኤል ያስወነጨፈ ሲሆን ጎላን ሃይትስ በሚገኙ በርካታ የግል መኖሪያ ቤቶችን አፍርሷል።

የሌባኖሱ ሄዝቦላ ከሃምሳ የሚበልጡ ሮኬቶችን ዛሬ ወደ እስራኤል ያስወነጨፈ ሲሆን፣ እስራኤል ወደ ግዛቷ በቀላቀለችው ጎላን ሃይትስ በሚገኙ በርካታ የግል መኖሪያ ቤቶች ላይ አርፏል።

ጥቃቱ የመጣው በጋዛው ጦርነት የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ከግብፅ እና ቃጣር አደራዳሪዎች ጋራ በተገናኙ ማግስት ነው።

የተኩስ አቁም ላይ ለመድረስ አሁንም አንዳንድ ችግሮች እንዳሉ እስራኤልም ሆነች ሐማስ በማስታወቅ ላይ ናቸው።

አዲስ የቀረበው ሃሳብ ከዚህ በፊት ቀርቦ የነበረውን ሃሳብ የቀየረ ነው ሲል ሐማስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። እስራኤል አዲስ ባቀረበችው ሃሳብ ላይ አሜሪካ ስምምነቷን ገልጻለች ሲል ሐማስ ክስ አሰምቷል።

እስራኤል ሌባኖስ ውስጥ ትላንት ማክሰኞ ባደረሰችው ጥቃት አንድ ሰው ተገድሎ 19 መቁሰላቸውን ተከትሎ በበቀል የተፈጸመ መሆኑን ሄዝቦላ አስታውቋል።

እስራኤል የሄዝቦላን መሣሪያ ማጠራቀሚያ ትላንት ማክሰኞ መምታቷን ተከትሎ፣ ሄዝቦላ ከ200 በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል አወንጭፏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG