በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስቅለት በዓል በእየሩሳሌም


በዛሬውለት በርካታ ክርስቲያኖች በዓለም ዙሪያ የስቅለትን በዓል በማክበር ላይ ናቸው። በእየሩሳሌም በዓሉ የተከበረው በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ እንደነበር ከኢየሩሳሌም ሮበርት በርገር ዘግቧል።

ከዓለም ዙሪያ የስቅለት በዓልን ለማክበር የተጓዙ ምእመናን፤ በምሳሌነት የእንጨት መስቀል ተሸክመው እየሱስ ክርስቶስ እንደተሰቀለበት ወደሚታመነው ቀራኒዮ አደባባይ በእግር ተጉዘዋል።

ከጥርብ ድንጋይ በተሰሩ ጠባብ Via Dolorosa ጎዳና አልፈው ወደ የመሪር ሃዘን በርን ሲሻገሩ ሃይማኖታዊ መዝሙሮችን ሲያዘሙና፤ መጸሃፍ ቅዱስ ሲያነቡ ታይተዋል።

በዚህ መልኩ ነበር 14ቱን የክርስቶስ መስቀል ያረፈባቸው ስፍራዎች ዛሬ በየሩሳሌም ምእመናን የጎበኙት።

“ያእቆብ አዴየሚ ከናይጀሪያ የመጡ ምእመን ናቸው። በመጸሃፍ ቅዱስ ታሪክ እየሩሳሌምና ስቅለት ትልቅ ስፍራ አላቸው።

“በስፍራው ተገኝቼ፤ ስቅለቱ የተፈጸመበትን ታሪካዊ ቦታ ስመለከት፤ ታላቅ ስሜት ነው ያደረብኝ።”

ዘንድሮ የምእመናኑ ቁጥር አነስተኛ ነበር። በተለይ በእየሩሳሌም ለስድስት ወራት የዘለቀ ሁከት ሰፍኖ ነበር። እስራዔላዊያን በፍልስጤማዊያን አጥቂዎች በስለት የመወጋት ጥቃት እንደደረሰ ሲዘገብ ቆይቷል። በዛሬው የስቅለት በዓል ላይ የእስራዔል ፖሊስ ባልደረቦች በሰፊው አደባባይ ወጥተው ታይተዋል። ከጣሊያን የመጡት ምእመን Emilio Carmone እየሩሳሌም የጦርሰራዊት ጣቢያ መስላለች ብለዋል።

“በለት ተለት ኑኖየ ዛሬ በየሩሳሌም ያየሁትን ያህል የጦር መሳሪያ አይነትና ብዛት ተመክቼ አላውቅም። ምናልባት ችግርና ሁከት ሊኖር እንደሚችል ተረድቻለሁ። እውነቱን ለመናገር የወታደሩና የጦር መሳሪያው ብዛት ደህንነት እንዲሰማኝ አላደረገም።” ብለዋል።

የሃይማኖታዊ ጉዞ በጥንታዊዋ ቅዱስ Sepulcher ቤተ-ክርስቲያን፤ ክስርስቶ የተሰቀለበት ስፍራ ላይ በምትገኘው ማህሌት ተጠናቋል። እሁድለት በርካታ ክርስቲያኖች የፋሲካን በዓልና የክርስቶስን ትንሳዔ ያከብራሉ።

የስቅለት በዓል በእየሩሳሌም
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG