በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል እና ሀማስ ነገ ሦስት ታጋቾች እና ዘጠና ፍልስጥኤማዊያን እሥረኞች ልውውጥ ያደርጋሉ


በጋዛ በሃማስ ታግታ የቆየችው የ29 አመቱ እስራኤላዊ አርቤል ዩሁድ እአአ ጥቅምት 7/2023
በጋዛ በሃማስ ታግታ የቆየችው የ29 አመቱ እስራኤላዊ አርቤል ዩሁድ እአአ ጥቅምት 7/2023

በጋዛው የተኩስ አቁም መሠረት ነገ ቅዳሜ በሚከናወነው አራተኛው የታጋቾች እና የእሥረኞች ልውውጥ እሥራኤል ዘጠና ፍልስጥኤማዊያን እሥረኞች እንደምትለቅ ተገለጸ። ሀማስ በበኩሉ ሦስት ታጋቾችን እንደሚለቅ አንድ የፍልስጥኤም ተሟጋች ቡድን ተናግሯል።

እሥራኤል ከምትለቃቸው ፍልስጥኤማዊያን መካከል ዘጠኙ የዕድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ሲኾኑ ሰማኒያ አንዱ ደግሞ የብዙ ዓመት እሥራት ቅጣት የተሰጣቸው እንደሆኑ የፍልስጥኤማዊያን እሥረኞች ክበብ የተባለው ቡድን ቃል አቀባይ አመልክተዋል።

ኪት ሲግል፥ ያርደን ቢባስ እና ኦፈር ካልደሮን የተባሉ ታጋቾች ነገ እንደሚለቀቁ የእስራኤል ባለስልጣናት እና ሃማስ አስታውቀዋል።

የታጋቾች ቤተሰቦች መድረክ የተባለው ቡድን በታጋቾቹ መለቀቅ ዜና መደሰቱን ገልጿል።

ትላንት ሐሙስ ሃማስ ስምንት ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤልም 110 ፍልስጥኤማዊያን ለቃለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG