በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሚችጋን ጠ/ፍ/ቤት ትረምፕ በክፍለ ግዛቱ ቅድመ ምርጫ እንዲቆዩ አደረገ


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ

በዩናይትድ ስቴትስ የሚቺጋን ክፍለ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞውን የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕን በግዛቱ ቅድመ ምርጫ እንዲቆዩ አደረገ።

ፍርድ ቤቱ ትረምፕ በቅድመ ምርጫው እንዳይቀርቡ ለሚፈልጉ ቡድኖች በስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ይግባኝ እንደማይሰማ ዛሬ ረቡዕ አስታውቋል።

ዛሬ የተሰጠው ውሳኔ እኤአ ታህሳስ 19 የኮሎራዶ ክፍለ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትረምፕ እኤአ ጥር 6 ቀን 2021 በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ህንጻ ላይ በተፈጸመው የአመጽ ጥቃት የነበራቸውን ድርሻ መሰረት በማድረግ በግዛቲቱ የቅድመ ምርጫ እንዳይሳተፉ ከሰጠው ውሳኔ በኋላ የተላለፈ ነው፡፡

የኮሎራዶው ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔውን የሰጠው በዩናይትድ ስቴትስ ህገመንግሥት 14ኛው የማሻሻያ አንቀጽ “በአመጽ ወይም በነውጥ የተሳተፉ ግለሰቦች የመንግሥት ሥልጣን እንዳይዙ የሚደነግገውን አንቀጽ በመጥቀስ ነው፡፡

የሚቺጋን እና የኮሎራዶ ክሶች ትረምፕን በየክፍለ ግዛቶቹ ቅድመ ምርጫዎች እንዳይሳተፉ ከሚደረጉ በርካታ ሙከራዎች መካከል እንደሚጠቀሱ ተመልክቷል፡፡

የሚችጋኑ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥያቄው በዚህ ፍርድ ቤት መታየት የሚገባው ስለመሆኑ አሳማኝ ሆኖ ያላገኘው መሆኑን አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG