በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማይክል ኮኸን የምስክርነት ቃል ይሰጣሉ


የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኸን
የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኸን

ለበርካታ ዓመታት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኸን ዛሬ እንደገና ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ተመልሰው ለደኅንነት ኮሚቴው የምስክርነት ቃል ይሰጣሉ። ኮሚቴው በዚህ ሳምንት በትረምፕ አስተዳደር ላይ አዲስ ምርመራ በከፈተውና ዲሞክራቶች በተቆጣጠሩት የተወካዮች ምክር ቤት ከሚገኙ በርካታ ኮሚቴዎች አንዱ ነው።

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የቀድሞ የግል ጠበቃ ማይክል ኮኸን ባለፈው ሳምንት ብቻ ሦስት ጊዜ በምክር ቤቱ ኮሚቴዎች ፊት ቀርበውበዝግና በግልጽ በተካሄዱ ስብሰባዎች ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ኮኸን በዚሁ ጊዜ “ፕሬዚዳንቱ ከሁለት ሴቶች ጋር ስለነበራቸው ግንኙነትና በሩሲያ ሊገነቡ ስለሞከሩት የንግድ ተቋም እንድዋሽላቸው አዘውኛል” ብለዋል።

ሚስተር ትራምፕ - ከሩሲያው መሪ ቭላዲሚር ፑቲን ጋር የነበራቸውንና ሊደብቁት የፈለጉትን ማናቸውንም ግንኙነት የሚያሳይ ሰነድ እንዲልክላቸው - ሦስት የተወካዮች ምክር ቤት ሊቃነ ማናብርት ትላንት በጋራ ሁዋይት ሃውስን ጠይቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG