በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማለዢያው MH17 አውሮፕላን ጉዳይ


ከአምስት ዓመታት በፊት የመከስከስ አደጋ የገጠመው የማለዢያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ 17ን ጉዳይ የሚመረምረው በዳች የሚመራው ቡድን፣ አዲስ ከስልክ ንግግር የተጠለፈ መረጃን ይፍ ማድረጉ ተገልጿል። መረጃው የሩስያ ወታደርዊ አዛዦች ከተገንጣይ ተዋጊዎችና ከክረምሊን ባለሥልጣኖች ጋር የተነጋገሩትን ያካትታል ይላል ቡድኑ።

ተጠለፈ የተባለው መረጃ ዛሬ የወጣው የዳቹ መርማሪ ቡድን በአውሮፕላኑ ላይ ለደረሰው አደጋ አዲስ ዕማኞችን ለማግኘት በሚያደርገው ጥረት ለመግፋት ነው ተብሏል። MH17 የተባለው አውሮፕላን ተከስክሶ ሲወድቅ በአውሮፕላኑ የነበሩት 298 ሰዎች በሙሉ ማለቃቸው የሚታወስ ነው።

በአደጋው እጃቸው አለበት የተባሉ 3 ሩስያውያንና 1 ኡክራይናዊ ኒዘርላንድስ ውስጥ ለፍርድ እንደሚቀርቡ የዳች አቃብያነ-ህግ ባለፈው ሰኔ ወር አስታውቀው ነበር። በሩስያ ባለሥልጣኖችና በምስራቅ ኡክራይን ይዋጉ በነበሩት ኃይሎች መካከል የቀጥታ የዕዝ መስመር እንደነበር የሚያሳይ ማስረጃ አለ ይላሉ አቃብይነ-ህጉ። ተገንጣይ የተባልው ቡድን “የዶኔትስክ ህዝባዊ ሪፑብሊክ” የተባለ እውቅና ያላገኘ መንግሥት መመስረቱን እንዳስታወቁ የሚያሳይ ማስረጃ እንዳለም አቃብያነ-ህጉ ጠቁመዋል።

MH17 አውሮፕላን እአአ ሐምሌ 17/ 2014 ዓም ላይ ከአምስት ዓመታት በፊት ማለት ነው ከአምስተርዳም ወደ ኩዋላላምፑር ሲበር የሩስያ ደጋፊ ተዋጊዎች በሚቆጣጠሩት ምስራቅ ኡክራይን ላይ መከስከሱ የሚታወስ ነው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG