በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜክሲኮ የቮልክስዋገን አፍቃሪዎች ሰልፍ አደረጉ


በሜክሲኮ ‘ቮቾ በመባል የሚታወቀው ጥንታዊ የቮልስዋገን በጎዳናዎች ላይ ሲንሸራሸር ሜክሲኮ፣ እአአ ሰኔ 23/2024
በሜክሲኮ ‘ቮቾ በመባል የሚታወቀው ጥንታዊ የቮልስዋገን በጎዳናዎች ላይ ሲንሸራሸር ሜክሲኮ፣ እአአ ሰኔ 23/2024

በሜክሲኮ ‘ቢትል’ የተሰኘችው የቮልክስዋገን ሞዴል አፍቃሪዎች፣ በሞዴሏ ዓለም አቀፍ ቀን በሆነው በትላንትናው ዕለት መኪናቸውን ይዘው ሰልፍ አድርገዋል።

በሜክሲኮ ‘ቮቾ’ ሲሉ የሚጠሯት ሞዴል፣ በኢትዮጵያም በብዛት ትታይ የነበረና አሁንም አጋጊጠው የሚነዷት እንዳሉ ይታወቃል።

አሮጌዋ ሞዴል ባላት ለየት ያለ ቅርጽ ተወዳጅነት በማትረፏ፣ በመላው ዓለም በሚገኙ ከተሞች በብዛት ትታይ ነበር።

ቢትል “የሕዝብ መኪና” ለመባልም በቅታ ነበር። በሜክሲኮ አሮጌዋ ሞዴል እ.አ.አ 2003 ድረስ፣ እስከ 20 ዓመት በፊት ድረስ መሆኑ ነው፣ ትመረት ነበር።

የቮልክስዋገን ኩባንያ አዲሶቹን ቢትል ሞዴሎች ከነጭራሹ ማምረት ያቆመው በእ.አ.አ 2019፣ ከአምስት ዓመታት በፊት ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG