የሜክሲኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርሴሎ ኤብራንድ 6,000 የሚሆኑ ወታደሮችን በድንበሩና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የማስፈሩ ተግባር ዛሬ ይጀመራል ብለዋል። ሁሉም ወታደሮች የሚመደቡበት ጊዜ መቼ እንደሆነ ግን አልገለጹም።
ሜክሲኮ ዩናይትድ ስቴትስ ለመግባት ሲሉ በግዛትዋ በኩል የሚያልፉትን ፍልሰተኞች ለመገደብ ከዩናይተድ ስቴትስ ጋር ባደረገችው ሥምምነት መሰረት ዛሬ ከጓቲማላ ጋር በሚያዋስናት ድንበር ላይ የብሄራዊ ዘብ ወታደሮችን ታሰፍራለች ተብሎ ይጠበቃል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ