ዋሺንግተን ዲሲ —
ሜክሲኮን በመታው ከባድ ርዕደ ምድር የሞቱት ሰዎች ቁጥር 286 ደረሰ፣ ገና ያልተገኙ ስላሉ የሟቾቹ ቁጥር ከፍ ሊል እንደሚችልም ተገለጸ።
ማዕከላዊ ሜክሲኮን ባናወጠውና በሬክተር መለኪያ 7.1 በተመዘገበው ርዕደ ምድር ከሞቱት ሌላ በሕይወት የተረፉትን ለማግኘት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሠራተኞች ቀንና ሌሊት ፍለጋችውን እንደቀጠሉ መሆናቸውም ታውቋል።
የሜክሲኮው ፕሬዚደንት ኤንሪኬ ፔና ኒየቶ የሦስት ቀናት ብሔራዊ ኃዘን አውጀዋል፣ በፍለጋው እየተጉ ያሉትንም አመስግነዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለማቀፍ የልማት ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ ከ60 በላይ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን፣ ልዩ ልዩ መድኃኒቶችንና የህክምና ቁሳቁሶችን ልኳል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ