በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች ከሱዳን በመተማ በኩል በመውጣት ላይ እንደኾኑ ተገለጸ


የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች ከሱዳን በመተማ በኩል በመውጣት ላይ እንደኾኑ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:43 0:00

የልዩ ልዩ ሀገራት ዜጎች ከሱዳን በመተማ በኩል በመውጣት ላይ እንደኾኑ ተገለጸ

በሱዳን በቀጠለው ግጭት፣ ሀገራት ዜጎቻቸውን ለማውጣት በሚያደርጉት ጥረት፣ ሱዳንና ኢትዮጵያን በሚያገናኘው መተማ - ገላባት ዋና መንገድ፣ የውጭ ሀገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ እንደኾነ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት እና የዐይን እማኞች ገለጹ፡፡

በዐማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ ከኻርቱም ተነሥተው በገላባት በኩል የሚገቡ የውጭ ሀገር ዜጎች፣ በድንበር አካባቢ በሕጋዊ መልኩ እንዲወጡ እየተደረገ ሲኾን፣ የጸጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው፣ ልዩ ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደኾነም አስታውቀዋል፡፡

በቀጣይም፣ ከካርቱም እና ከሌሎች የሱዳን ክፍላተ ግዛት ተፈናቅለው ለሚመጡ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የሱዳን ሕዝብ፣ የአካባቢው ባለሥልጣናት ከረድኤት ድርጅቶች ጋራ በመተባበር የማረፊያ ስፍራ በመዘጋጀት ላይ መኾኑን አቶ ቢክስ አመልክተዋል፡፡

ከሱዳን ጋራ ከሚዋሰነው የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ እና በአቅራቢያው ከሚገኙ ከተሞች ከሚኖሩየዐይን እማኞች፣ ከእሁድ ጀምሮ፣ መቶ ያህል የውጭ ሀገር ዜጎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች፣ የሱዳንን ድንበር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ በበኩሏ፣ ዜጎቿን ከሱዳን ለማስወጣት እገዛ ለአደረጉ ሀገራት ምስጋና አቅርባለች፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG