በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመተማ አርሶ አደሮች "የሱዳን ታጣቂዎች አፈናቀሉን፤" አሉ


- "246 ባለሀብቶች ሥራ አቁመዋል" /የዞኑ አስተዳዳሪ/

ከሱዳን ጋራ በሚዋሰነው የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማወረዳ፣ ሽመት መገዱቃ በተባለ ቀበሌ፣ ባለፈው ሳምንት በሱዳን መንግሥታዊ ታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት፣ የግብርና እንቅስቃሴያቸው እየተስተጓጎለባቸው እንደኾነ፣ በዘርፉ የተሠማሩ ባለሀብቶች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታወቁ።

በአካባቢው ላይ እየተፈጸመ በሚገኘው ተደጋጋሚ ጥቃት፣ በአንድ ዓመት ውስጥ በእርሻ ሥራ ላይየተሰማሩ 246 ባለሀብቶች ሥራቸውን እንዳቆሙ፣ የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ የጠየቃቸው የሱዳን ጦር ቃልአቀባይ ኮሎኔል ናቢልአብደላ፣ ትናንት ለብዙኀን መገናኛ መረጃ መስጠታቸውን አውስተው፣ ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልኾኑ ገልጸዋል።

ቃለ አቀባዩ የሰጡትን ምላሽ እንድንመለከት የጠቆሙን "ሱዳን ፕላስ" የተሰኘ የዜና አውታር፣ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ናቢል፤ የሱዳን ኃይሎች በድንበር አካባቢ መደበኛ ቅኝት እንደሚያደርጉ ፤ አልፎ አልፎ ግን ከኢትዮጵያ የሚሊሺያ ኃይሎች ጋራ ግጭት እንደሚያጋጥም መናገራቸውን ዘግቧል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ/

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:43 0:00

XS
SM
MD
LG