የኢትዮጵያ መንግሥት በሙስናና ሰብዓዊ መብት ጥሰት ጠርጥርያቸዋለሁ ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ሥር እያዋለ ይገኛል ይህ ጉዳይም መነጋገርያ ሆኗል።
በዚህ ጉዳይ አስመልክቶ የአቋም መግለጫ ያወጣ የትግራይ ክልል መንግሥት የክልሉ ህዝብና መንግሥት የህግ ልዕልና እንዲሰፍን አበርትተው ይሰራሉ ብሏል። እንዲሁም በሙስናና ሰብዓዊ መብት ጥሰት እየታየ ያለ ሁኔታ አንድ ብሄር መሰረት እንዳያደርግ እንታገላለን ሲል ገልፅዋል፡፡
በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ስትራቴጂካዊ ጥናት አስተማሪ አቶ ሰይፈ ኃይሉ እየተወሰደ ያለው እርምጃ የሕግ ልዕልና ከማስከበር ይልቅ ፖለቲካዊ መልክ የያዘ የትግራይ ሊህቃን ለማጥፋት ያለመ ነው ብለው እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
የዓረና ለሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ብሔር መሰረት ያደረገ ነው ብለህ ለመናገር የሚያስደፍር አይደለም ብለዋል።
ሰብ ሕድሪ የተባለ ሲቪል ማሕበረሰብ በበኩሉ በጥናትና ሚዘናዊ የሆነ የህግ ተጠያቂነት መኖር አለበት ብለን እናምለን በማለት የገለፀ ሲሆን ሆኖም ግን በአሁኑ ግዜ በአገሪቱ በህግ ልዕልና ስም የትግራይ ተወላጆች የማዳከም ሥራ እየተሰራ መሆኑን እንደሚገነዘብ አስታውቋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ