በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘከርበርግ የ'ትሬድ'ን ፍሊሚያ ወደ አውሮፖ ህብረት ወሰዶታል

በዩናይትድ ስቴትስ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኢንዱስትሪ ትልቅ ስም ያለው ማርክ ዘከርበርግ፣ አዲሱን 'ትሬድ' የተሰኘ መተግበሪያ አውሮፖ ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች በመከልከል፣ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችል እና የአውሮፓ ህብረትን እጅ መጠምዘዝ የመሰለ አደገኛ ፍልሚያ ውስጥ ገብቷል።

በኢላን መስክ አመራር ቀውስ ውስጥ የገባውን ትዊተር እያሽመደመደ እንደሆነ እየተገለፀ ያለው ትሬድ መተግበሪያ፣ በመጀመሪያው ሳምንት ብቻ ከ100 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ተቀላቅለውታል።

ዘከርበርግ የሚመሩት ሜታ ኩባንያ በአውሮፓ እስከሚቀጥለው አመት ድረስ ተግባር ላይ የማይውለው የዲጂታል ገበያ 'ቁጥጥር እርግጠኛ ባለመሆኑ' መተግበሪያው ለአውሮፓ ጥቅም ላይ መዋል አልቻለም ብሏል።

"የሰጡኝ ምክንያት አስቆኛል" ያሉት የአውሮፓ ዲጂታል መብቶች የተሰኘ አቀንቃኝ ቡድን የፖሊሲ ሀላፊ ዲያጎ ናራንጆ "ደንቡ አጠራጣሪ አይደለም። እሙን ነው። ችግሩ ሜታ ያልወደደው መሆኑ ብቻ ነው" ብለዋል።

ዘከርበርግ አላማቸው ትሬድን ለመላው ዓለም አቅርበው ለአውሮፓ በመከልከል፣ አውሮፓውያን ተለይተው በመቅረታቸው ተበሳጭተው በአውሮፓ ህብረት ላይ ተፅእኖ እንዲያሳድሩ በማድረግ፣ የዲጂታል ገበያ ቁጥጥሩን ማላላት ነው። ናራንጆ ግን ይህ ዘዴ አይሳካም ይላሉ።

ሜታ እና ሌሎች ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ በግለሰቦች መረጃ አሰባሰብ እና አጠቃቀም ፖሊሲዎቻቸው ዙሪያ ከአውሮፓ ህብረት ተቆጣጣሪዎች ጋር ችግር ውስጥ ገብተዋል።

የዲጂታል ገበያ ህጉ ተቋማቱ ስምምነት እስካላገኙ ድረስ የግለሰቦችን መረጃ ከአንድ መተግበሪያ ወደ ወደ ሌላ እንዳያስተላልፉ ይከለክላቸዋል።

ኢንስታግራም ከተሰኘው መተግበሪያ ጋር ተጣምሮ ለተሰራው 'ትሬድ' ደግሞ ይሄ አስቸጋሪ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG