በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ


አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ
አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ አቶ መስፍን ጣሰው በቀለን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

አቶ መስፍን የተሾሙት በጤንነት እክል ምክንያት ራሳቸውን በጡረታ ማግለላቸው በተገለጸው የቀድሞ የአየር መንገዱ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ምትክ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ አቶ መስፍን በአየር መንገዱ ውስጥ የ38 ዓመታት ልምድ ያላቸው መሆኑን ተገልጿል፡፡

በአየር መንገድ አገልግሎታቸው በአስተዳደር፣ በአውሮፕላን ጥገና፣ በምህንድስና፣ በእቃ ግዥ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በበረራ ኦፐሬሽን፣ አቅም ግንባታና በኮፖሮሬት አመራር ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ መሆኑንም መግለጫው አመልክቷል፡፡

አቶ መስፍን ካለፈው ዓመት ጀምሮ የአየር መንገዱ እአአ ከ2010 እስከ 2021 ድረስ የአየር መንገድ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የፖን አፍሪካ አየር መንገድ ብሎ ራሱን የሚጠራው የተለያዩ ምዕራብ አፍሪካ አገሮች አየር መንገድ ASKY ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን አየር መንገዱን ለአትራፊነት ያበቃ አመራር የሰጡ መሆኑን መግለጫው አመልክቷል፡፡

አቶ መስፍን በቢዝነስ አስተዳደር የማስተስር ዲግሪያቸውን ከእንግሊዝ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ኮሙኒኬሺን ኢንጂነሪንግና የማስተርስ ዲግሪያቸውን፣ በኤሌክትሪካል ኤንጂነሪንግ ደግሞ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ማግኘታቸውን መግለጫው ጠቅሷል፡፡

XS
SM
MD
LG