መሠረት ደፋር በስቶክሆልም ዳያመንድ ሊግ በ 3 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር የዓመቱን የዓለም ፈጣን ጊዜ በማስመዝገብ አሸንፋለች። በሉዥኒኪ ሞስኩ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ 5 ሺህ የወርቅ ሜዳልያ ከወሰደች ከሁለት ሳምንት ባነሰ ጊዜ መሆኑ ነው መሠረት ይህን ድል የተቀዳጀችው።
በሐሙሱ የዳያመንድ ሊግ 3 ሺህ ሜትር አዲሱ የመሠረት ደፋር የዓመቱ ፈጣን ጊዜ 8 ደቂቃ ከ 30 ነጥብ 29 ሴኮንድ ነው።
ሌላዋ የኢትዮጵያ አትሌት ሲፋን ሐሰን የግሏን ፈጣን ጊዜ አስመዝግባ በሦስተኝነት ጨርሳለች።
መርሲ ቼሮኖ ከኬንያ የብሩን ሜዳልያ አጥልቃለች።
በሐሙሱ የዳያመንድ ሊግ 3 ሺህ ሜትር አዲሱ የመሠረት ደፋር የዓመቱ ፈጣን ጊዜ 8 ደቂቃ ከ 30 ነጥብ 29 ሴኮንድ ነው።
ሌላዋ የኢትዮጵያ አትሌት ሲፋን ሐሰን የግሏን ፈጣን ጊዜ አስመዝግባ በሦስተኝነት ጨርሳለች።
መርሲ ቼሮኖ ከኬንያ የብሩን ሜዳልያ አጥልቃለች።