በኢትዮጵያ ትልቁ በሆነው በመርካቶ ገበያ በተለይ ከሰኞ ጀምሮ ሲተገበር የነበረው ሱቅ የመዝጋት አድማ ዛሬ በአብዛኛው ቆሟል፡፡
የቪኦኤ ዘጋቢ ወደገበያ ስፍራው ተጉዞ ባደረገው ቅኝት እንደተመለከተው፣ ሱቆች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተከፍተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሥልጣናት፣ ችግሩን ለመቅረፍ ከመርካቶ ነጋዴዎች ጋራ ከትላንት በስትያ ውይይት አድርገዋል፡፡
ሆኖም ዛሬ ሱቆች የተከፈቱ ቢሆኑም፣ ብዙም ግብይት አይስተዋልም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ፣ ሸማቾችም ወደ ገበያው ብዙም ጎራ አለማለታቸው እንደሆነ አስተያየታቸውን የሰጡ ነጋዴዎች ተናግረዋል፡፡
መድረክ / ፎረም