አዲስ አበባ —
ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ እንዲፈቱ ጠበቆቻቸው ያቀረቡት ጥያቄ በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች መሠረት ውድቅ ይደረግልኝ ሲል ፌደራል ዓቃቤ ሕግ አመልክቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ ጉዳዮን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለነገ መጋቢት 1/2009 ዓ.ም. ቀጥሯል፡፡
ዓቃቤ ሕግ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ባቀረበው የፁሑፍ አቤቱታ በባለፈው ሣምንት ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ ተፈትተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠበቆቻቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ተቃውመ፡፡
ዓቃቤ ሕግ በፃፈው በዚህ የተቃውሞ ማመልከቻ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተያዙ ሰዎች በዋስትና የመፈታት መብት ቢኖራቸውም በሕግ በተደነገጉ ልዩ ሁኔታዎች ፍርድ ቤት ዋስትና ላለመቀበል ይችላል ሲል ይንደረደራል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ