አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ያለው 13ኛው የዓለም የጤና አጠባበቅ ማኅበራት ፌዴሬሽን ጉባዔ ኢትዮጵያዊውን ዶ/ር መንግሥቱ አስናቀን ለሁለት ዓመታት ም/ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል፡፡
በፌዴሬሽኑ ደንብ መሠረት ዶ/ር መንግሥቱ ከሁለት ዓመታት በኋላ ያለሌላ ምርጫ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ፡፡
ዶ/ር መንግሥቱ አሁን ፓዝፋይንደር ኢንተርናሽናል የሚባለው ግብረሰናይ ድርጅት የኢትዮጵያ ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር ሲሆኑ ቀደም ሲል የኢትዮጵያ የጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለዋል፡፡
በሙያቸው ሐኪም የሆኑት ዶ/ር መንግሥቱ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
ስለዶ/ር መንግሥቱ አስናቀ ማንነት ይበልጥ ለማወቅ ቃለምልልሱን ያዳምጡ፡፡