በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መለስ ዜናዊ በአፍሪካ ኢኮኖሚ መንግስቱ መሪ ድርሻ እንዲኖረው ያቀረቡት ሀሳብ ሲተነተን


የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አፍሪካ አዲስ የልማት ግብና እቅድ ሊኖራት እንደሚገባ በአዲስ አበባ ለተሰበሰቡ የአፍሪካ የገንዘብ ሚኒስትሮች መክረዋል።

በዚህ በአዲሱ የልማት ግብ መንግስት በግሉ ዘርፍ የተያዙ ወይንም ሊያዙ የሚችሉ አውታሮችን በመተካትና በበላይነት በመምራት፤ አህጉሪቱን ወደተሻለ የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ይቻላል ብለው አቶ መለስ ያምናሉ።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር አዲስ አይደለም፤ ከዚህ በፊትም በተለያዩ የኢኮኖሚ ውይይት መድረኮች ላይ እሳቸውና ተመራማሪዎች ኒዮ-ሊብራሊዝም የሚሉትን በነጻ ገበያና በግል ዘርፉ የኢኮኖሚ መሪነት የሚያምን ስልት “ውድቋል” ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ መለስ ለአፍሪካ ዘለቄታ ያለው እድገት ያመጣል የሚሉት

መንግስት በግሉ ዘርፍ የተያዙ ወይንም ሊያዙ የሚችሉ አውታሮችን በመተካትና በበላይነት በመምራት ኢኮኖሚው ላይ የመሪነት ሚና እንዲኖረው የሚያስችል ነው።

ለሰላሳ አመታት በአለም ባንክ ያገለገሉና አራተኛ መጻህፋቸውን በመጻፍ ላይ ያሉት ዶክተር አክሎግ ቢራራ የአቶ መለስ አባባል ቅንጣት እውነት ቢኖረውም በአጠቃላይ ኢኮኖሚው በመንግስት እጅ ከወደቀ፤ ገበያው ቅልጥፍናን ተወዳዳሪነት ይጎድለዋል ይላሉ።

(ከዶክተር አክሎግ ጋር የተደረገውን ውይይት ያዳምጡ)

XS
SM
MD
LG